የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ ጋር ውይይት አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ ጋር ውይይት አደረጉ

ሰኔ 27/2017 (የሰላም ሚኒስቴር)፤ ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ ጋር በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጥረቶችን ለማገዝ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ውስጥ አሁን ላይ እየታየ ያለው አንፃራዊ ሰላም እንዲመጣ መንግሥት ያደረገውን ሰፊ ጥረት አስገንዝበው፤ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላምን ለማጽናትና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ መንግሥት ከሕዝቡ ጋር እየሠራ ያለውን ሥራ አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ዋና የምርጫ አስፈፃሚ የሆኑት አኪን ያሚን የሰላም ሥራዎች ለሀገራዊ ምርጫው ታላቅ ትርጉም አንዳላው ጠቅሰው፣ በመንግስት የሚሰሩ ሰላምን የማፅናት ስራዎችን እንደሚደግፉ አመላክተዋል፡፡