የሰላምና ልማት የመንግስታት ግንኙነት ውይይት ተካሄደ
የሰላምና ልማት የመንግስታት ግንኙነት ውይይት ተካሄደ
የሰላም ሚኒስቴር የጋምቤላ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ክልሎች የሰላምና የልማት የጋራ የመንግስታት ግንኙነት የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

ውይይቱን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማህበር ኮር የከፈቱት ሲሆን ዓላማውም ከዚህ በፊት በሁለቱ ክልሎች አጎራባች በሆኑ ሸካ ዞን እንደራቻ ወረዳና ማጃንግ ዞን መንገሽ ወረዳ የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት የተቋቋሙ የጋራ የእርቀ ሰላም አፈላላጊ የሀገር ሽማግሌዎች ስራዎችን ለመገምገም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡


መድረኩ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን በተለይ በማጃንግ ዞን መንገሺ ወረዳ እና በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ አዋሳኝ በሆነው ልዩ ስሙ ጂ-ፎር በተባለው አካባቢ ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የተዋቀረው ኮሚቴ የሰራውን ሥራ ለመገምገምና ችግሮችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው፡፡
በውይይቱ የተቋቋሙት የእርቀ ሰላም አፈላላጊ የሃገር ሽማግሌዎች ሪፖርት አቅርበው ላጋጠሙ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡ ውይይቱን የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩ ጌታ ገነነ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች፣ ከሁለቱም ክልሎች የተወጣጡ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከፍተኛ ሃላፊዎችና ከሁለቱም ወረዳ የተጋበዙ የሃገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል፡፡