በስርዓተ-ትምህርት ውስጥ የሰላም ትምህርት እንዲካተት ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር ከአፍሪካ ሴቶች የሰላምና ደህንነት ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር በስርዓተ-ትምህርት ውስጥ የሰላም ትምህርት እንዲካተት ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ ወንድወሰን መኮንን በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሰላም ትምህርት የሀገር ግንባታ ስራችን አምድ የሆነው ሀገራዊ ሰላማችንን የምናፀናበት፤ ሀገራዊ ስሜቱ የጎላ ትውልድን የመገንባት በመሆኑ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም የነጣጣይና ከፋፋይ ትርክት ስብራታችንን ለመጠገን፣ የጋራና የአብሮነት ትርክታችንን ለማከም እና ግጭትን የሚጠየፍና ምክንያታዊ ትውልድን ለመገንባት የሰላም ትምህር ቁልፍ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

መድረኩ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም ጉዳይ የነበሩ ክፍተቶችን በማረም የሠላም ባህል ግንባታን ለማዳበር የሰላምን ዋጋ ልጆች ከመዋዕለ ህጻናት ጀምሮ እንዲረዱት ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ በስርዓተ ትምህርት ውስጥ በማካተት ለማስተማር ያለመ መሆኑ ተ ገልጿል ።

በምክክር መድረኩ የትምህርት ሚስቴር፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩትን ጨምሮ ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።