የሰላም ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ13ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ሰልጣኞችን አስመረቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 4/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በ13ኛው ዙር መርሃ ግብር ያሰለጥናቸውን የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ተሳታፊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አስመርቋል።

በምረቃ ስነ-ሥርዓቱ ተገኝተው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አማካሪ አቶ ፍሬሰንበት ወልደተንሳኤ የሰላም ሚኒስቴር ከ2013 ዓመት ጀምሮ ለተከታታይ 12 ዙሮች “በጎነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ሃሳብ የጀመረው የወጣቶች በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት መርሐ-ግብር ኢትዮጵያዊ እሴቶችን እና መርሆችን ለወጣቱ ትውልድ በማስተላለፍ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት እና በሌሎችም ማንነቶች ላይ መሠረት አድርጎ ያለውን መከፋፈልና ጥርጣሬ በማስወገድ የወጣቶችን የሀገር እና የሕዝብ ፍቅር ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፆ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሂደቱም በጎ ፈቃደኞች የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣታቸው፣ በማህራዊ ትስስር፣ በስራና ፈጠራ፣ ብዘሃነትን በማስተናገድ እና የሀገር ፍቅርን በማሳደግ፣ የሰላም አምባሳደሮች የተፈጠሩ ሲሆን፤ በብቃታቸውና ስነ-ምግባራቸው የተሻሉ ዜጎችን ማፍራት ከመቻሉም ባሻገር ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፆ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ፍሬሰንበት አያይዘውም በዓለም በበጎ ፈቃድ ስራቸው ተምሳሌት የሆኑ ግለሰቦችን ጠቅሰው፤ በበጎ ፈቃድ ስራ ላይ መሳተፍ ዕድለኝነት እና የህሊናና የመንፈስ እርካታ የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ ወጣቶች ማህበረሰባዊ እሴቶችን በመጠበቅ እና የሞራል አቅማቸውን በማጎልበት ከጭፍን ጥላቻ የወጣ እርስ በርስ የተጋመደ ማህበረሰብ እንዲፈጠር በማድረግ በዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት ስራ ውስጥ የራሳችውን አሻራ እንዲያሳርፉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለዚህ ስልጠና መሳካት የማይተካ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሰላም ሚኒስቴር ስም ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ለተመራቂዎች መልካም የአገልግሎት ጊዜን ተመኝተዋል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አወል ሰይድ የሰውነት መነሻው በጎነት በመሆኑ በየትኛውም የህይዎት ጎዞ በጎነትን ማሰብ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን፤ በጎነት ሲመቸን ወይም ሲሞላልን የምንሰራው ሳይሆን ባለንበት በማንኝውም ሁኔታ ዋጋ በመክፈል የምንፈጽመው ማህበራዊ እሴት ነው ሲሉ በህይዎት ጉዟቸው ያጋጠሟቸውን የበጎ ሰዎች ስራ በመጥቀስ ለተመራቂዎች አካፍለዋል።

በስነ-ሥርዐቱ ከዞን ከክልል፣ ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የሀገር ሽማግሌዎች የተገኙ ሲሆን፤ በስልጠናው አስተዋጾ ላበረከቱ አካላት የአማራ ክልል የለላምና ፀጥታ ቢሮ ምከትል ኃላፊ በሆኑት ኮሚሸነር ደጀኔ ልመንህ ሰርተፍኬት ተሰጥቷል። የምረቃ ስነ-ሥርዐቱ በሃይማኖት አባቶች ቡራኬ ተጀምሮ በባህል ውዝዋዜዎች፣ በመነባንብ እና ጭውውቶች የደመቀ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመዘመር ተጠናቋል።