የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ግንቦት 19/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር በሰላም ግንባታ፣ በግጭት አስተዳደርና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ መንግስት ዘላቂና አዎንታዊ ሰላምን ለመገንባት፣ ግጭትን አስቀድሞ ለመከላከልና ለማስተዳደር እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር ) በበኩላቸው በሀገራችን የውይይት ባህልን ለማጎልበትና በተለይ ወጣቱ የሰላም ባለቤት እንዲሆን የሚያስችሉ የወሰን ተሻጋሪ የሰላም በጎ ፈቃድ ስራ ተግባራትን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በስፋት እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተገኙ ኃላፊዎች ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው መንግስት የተረጋጋና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የመመለስና መልሶ የማቋቋም እንቅስቃሴ ላይ እያከናወነ ያለውን ተግባር አድንቀው ለዚህም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ፍላጎታቸውን አሳይተዋል፡፡