ለሃይማኖት ተቋማት አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ግንቦት 14/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለሃይማኖት ተቋማት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የሃይማኖት ተቋማትና መንግስት በዘላቂ ሰላም እና በሀገር አንድነት ላይ አብረው እየሰሩ እንደሚገኝ ገልፀው የሃይማኖት ተቋማት ሰላም እንዲሰፍን፣ በህዝቦች መካከል አብሮነት እንዲጠነክርና አገራዊ መግባባት እንዲሰፍን ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም የሰላም ሚኒስቴር በሐይማኖቶች መካከል የዳበረ ግንኙነትና መከባበር እንዲኖር፣ የሐይማኖት ተቋማትና መንግሥት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሰሩ እና የሐይማኖት ተቋማት በሰላም ግንባታና አብሮነት ላይ ሚናቸው እንዲወጡ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የዛሬው ስልጠና ዓላማ ለሃይማኖት ተቋማት አባላት በፕሮቶኮልና ኢቲኬትስ፣ በኩነት ዝግጅትና አስተዳደር፣ በሚዲያ አጠቃቀምና ሞኒተሪንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት የሃይማኖት ተቋማት በተለያዩ ሀገራት ሲንቀሳቀሱ እና የተለያዩ ሀገራትን እንግዶች ሲቀበሉ ፕሮቶኮሉን ጠብቀው ሀገራቸውን እንዲያስተዋውቁ ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትን ወክለው ንግግር ያደረጉት አቶ መላኩ ሙላለም ተቋማቸው እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡