የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዢህ አላመሐመዲ ጋር በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ ተወያዩ
የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዢህ አላመሐመዲ ጋር በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ ተወያዩ
መጋቢት ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፤ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዢህ አላመሐመዲ ጋር በተጀመሩ የሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡
የሁለቱን ሀገራት ጥቅምና መብት ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ልምድንና እውቀትን በማቀናጀት ለሰላም ግንባታ ስራዎች ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አድርገዋል፡፡
ሚኒስትር ዴዔታው ተቋሙ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና ልዩነቶችንም በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ልምድ እንዲገነባ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ለአምባሳደሯ ገልፀዋል።
ሁለቱ እህትማማች ሀገራት ጥንታዊ ታሪክና ብዝሀነት ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴዔታው ብዝሀነትን በአግባቡ በማስተዳደር ዘላቂ ሰላምን በመገንባትና አካታች ብልፅግናን በማረጋገጥ ረገድ በጋራ መስራት እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።
የሞሮኮ አምባሳደር ነዢህ አልመሀመዲ በበኩላቸው ኢትዮጵያም ካላት ረጅም ታሪክ በተለይ በሀይማኖቶች መካከል የዳበረ የመከባበር ባህልና ከሀገሪቱ ብዝሀነት አቅም በርካታ ተሞክሮ መውሰድ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።
ሁለቱን ጥንታዊ ሀገራት ብዝሀነትን በአግባቡ በማስተዳደር የተረጋጋ ሰላምን በማምጣትና ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት ተቀራርቦ ለመስራት ፤ በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩም አምባሳደሯ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።