ሚዲያዎች በሰላምና በሀገር ግንባታ መሰረታውያን ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ተባለ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ከቅን ልቦች በጎ ስራ ድርጅት ጋር በመተባበር "የሀገር ግንባታ መሰረታውያን" በሚል ርዕስ ከማህበረሰብ አንቂዎች ጋር  ምክክር አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ የሰላም ሚኒስቴር ሀገራዊ መግባባትንና አንድነትን በማሳደግ ሁለንተናዊና ዘላቂ ሰላም መገንባት ተልዕኮ የተሰጠው በመሆኑ የሀገራችን ዘርፈ ብዙና ውስብስብ የሰላም ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ ሁሉን አቀፍ ምክክርና ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

 

በዛሬው ዕለትም ከማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ጋር በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ ለዘላቂ ሰላም ግንባታን በማጎልበት በተዋረድ በማህበረሰቡ ውስጥ ንቅናቄ ለመፍጠር የሚያስችል ምክክር እየተካሄደ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

የሀገር ግንባታ ጥረታችን በጅምር ላይ ያለና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ሰፊ ስራን የሚጠይቅ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የሀገር ግንባታ ስራ የመንግስት፣የትምህርትና የእምነት ተቋማት፣የሚዲያ አካላት እንዲሁም የዜጎች የተቀናጀና የተናበበ የጋራ ጥረትና ሃላፊነት መወጣትን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገር ግንባታ ስንልም በእያንዳንዱ ዜጋ አዕምሮ እና ልብ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ማንነት የመቅረጽ ተግባር ነው፡፡ ይህ ተግባርም ቸል ሳይባል የሁል ጊዜ ተግባር ተደርጎ ሁሉም በተሰማራበት የሙያ መስክ ሊገነባው የሚገባ ጉዳይም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

ክቡር አቶ ታየ ሀገራዊ መግባባትን ለማጎልበት እንደ ሀገር ሀገራዊ ማንነትን፣እሴቶችን እና ሀገራዊ ጥቅሞችን ለይቶ ማወቅና እንደ ዜጋ የጋራ ማድረግ የሚጠይቅ ሲሆን የሚዲያ አካላትም እነዚህን የሀገር ግንባታ መሰረታውያን ማወቅ፣ማስተዋወቅ ብሎም ማስረጽ ትልቅ ሃላፊነት የሚወስዱበት ተልዕኮ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

                                              

የዛሬው የውይይት መድረክ ዓላማ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በማጎልበት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ መደላድል ለመፍጠር ነው ተብሏል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የብሄራዊ መግባባት ዴስክ ሀላፊ አቶ ገዛኝ ጥላሁን "የሀገር ግንባታ መሰረታውያን ሀገራዊ ማንነት፣እሴትና ጥቅም ግንባታ" የሚል ጹሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሄዷል፡፡

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ክቡር አቶ

ታየ ሰላም በጦርነት አይመጣም፡፡ ስለሆነም ችግሮቻችንን በንግግርና በድርድር መፍታት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምትሰሩ አካላት አንዱ ሌላውን እያጋጩ መነገድ የለበትም ይህም መታረም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በሀገር አንድነትና ሰላም ላይ መደራደር እንደማይገባም አሳስበዋል፡፡