የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ከሞሮኮ ልዑካን ጋር ተወያዩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 17/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የሞሮኮ ልዑካንን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በሞሮኮው መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ሰክሬተሪ ዶ/ር መሐመድ ረፊቅ የሚመራው ልዑክ ከሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ጋር የሁለቱን ሀገራት መልካም ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ የቀደመ ስልጣኔ ያላት ጥንታዊት ሀገር እንደመሆኗ ብዙ ልምዶችን ማካፈል እንደምትችል በማሰብ ለልምድ ልውውጥ መምጣታቸውን የገለጹት ልዑካኑ በብዝኃነት አያያዝ በተለይም ቤተ እምነቶች በሰላም እና በአብሮነት ለጋራ ሰላም እና ተጠቃሚነት የሚሠሩበት ሁኔታ ለሀገራቸው ሞሮኮ ጥሩ ልምድ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሁሉንም ሃይማኖቶችና እምነቶች በእኩልነትና ፍትሐዊነት የምታስተናግድበት ሕገ መንግሥት መኖሩ፤ ከአድሏዊነት ነፃ የሆነ የመንግሥት አገልግሎት የሚሰጥበት ሥርዓት መዘርጋቱ በመካከላቸው ሰላማዊ የሆነ ግንኙነት ማጠናከሩን ክቡር ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ በውይይቱ ወቅት ገልፀዋል።

ልዑካኑ የሞሮኮ መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን በ48 የአፍሪካ ሀገሮች ቅርንጫፎችን የከፈተ መሆኑን በመግለጽ በኢትዮጵያም ቅርንጫፍ ለመክፈት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

 

ክቡር ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው ሚኒስቴር መ/ቤቱ የቀረበውን ቅርንጫፍ የመክፈት ጥያቄ በመመልከት ወደ ፊት ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

                                                                                                                               ሰላም ለኢትዮጵያ !