የሀይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሰላም እሴት ግንባታ ላይ በመስራት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡ ተጠየቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር “የሀይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለሰላም ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫና የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የሀይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሀይማኖታዊ አስተምህሮቶችን ለተከታዮቻቸው ከማስተማር ባለፈ መልካም ስነምግባርን በማስረጽ፣ መተሳሰብና አብሮነትን በማጎልበት በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ያተኮረ ቋሚ ፕሮግራም በማዘጋጀት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ክቡር አቶ መሀመድ የሀይማኖት ተቋማት ሀገርን በመጠበቅና በመገንባት ወደፊትም ከፍ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ያላቸው በመሆኑ በሚያስተዳድሯቸው የመገናኛ ብዙኃን ትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ በበኩላቸው መድረኩ ለሀገር ሰላምና አንድነት መጎልበት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መሆኑንም ገልጸዋል።

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) "የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ለትውልድ ግንባታና ለአገር ሰላም መጠናከር ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ እድሎች መሆናቸውን ጠቅሰው ተቋማቱ በመከባበርና በትብብር በመስራት ለአገራዊ አንድነትና ለሰላም አርአያ ሊሆኑ ይገባል" ብለዋል፡፡

በመድረኩ "የሀይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና" በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ በዶ/ር አንተነህ ጸጋዬ የቀረበ ሲሆን "የሀይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ዙሪያ በመስራት ረገድ የሚገኙበት ሁኔታ" ደግሞ ከመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአቶ ደሬሳ ተረፈ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አመራሮች፣ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።