ህዝባዊ ኮንፈረንስ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፤ በሱማሌ እና አፋር ክልሎች ተከስቶ የነበረውን ግጭትን በዘላቂነት ለመፍታት በክልሎቹ ሲካሄድ የቆየው የእርቀ ሰላም ውይይት በሱማል ክልል ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡

በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ተከታታይ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች ሲካሄዱ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተደረገው ኮንፈረንስ የነበረውን ግጭት በእርቀ ሰላም ቋጭቶ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እና ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ያለመ ነው።

በሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በሁለት ወንድማማች ሕዝብ መካከል የተፈጠረው ግጭትም ሆነ በግጭቱ ምክንያት የተከሰተው ጉዳት ፍጹም መከሰት የሌለበት መሆኑን ገልፀው ችግሩን በእርቀ ሰላም ቋጭቶ ቁርሾ መሻር፣ በክልሎቹ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን መሥራት እና ወደ ሰላም መሸጋገር ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የተደረጉ ውይይቶች የሕዝቡን ሰላም ወዳድነት በጉልህ ያንፀባረቀ መሆኑን ጠቅሰው ግጭትን በማስቀረት የተፈናቀሉ ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ የሆነ እና የተረጋጋ ሕይወት እንዲጀምሩ አሳስበዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ግጭቶች በወንድማማችነት በሰላማዊ ንግግር የሚፈቱበትን አመለካከት በሕዝቡ ውስጥ ማስረጽ እና ዳግም መሰል ችግሮች እንዳይፈጠሩ ፤ እንዲሁም የሕዝብ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲጎለብት እገዛና ትብብር የሚጠይቅ ስለሆነ በየደረጃው ሁሉም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የሱማሌ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አህመድ በአፋርና ሱማሌ ክልሎች በማኅበረሰቦች መካከ በተለያዩ ጊዜያት ሲነሱ የነበሩ ግጭቶች በሰው፣ በንብረት፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚ ላይ ብዙ ጉዳት ያስከተለ እና ሕዝቡን በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳው መሆኑን አስገንዝበው ለግጭት ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን መከላከል እና ለሰላም በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በክልሎቹ መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ እና መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ ተገቢ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

ችግር የተፈጠረባቸውን አካባቢዎች ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ፣ ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር እና የጋራ ሰላማቸውን ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እናቶች ልጆቻቸውን ለመጠበቅ ፣ ዳግም ወደ ግጭት የሚያመሩ እንቅስቃሴዎች ሲታዩ በሰላማዊ ውይይቶች ለመፍታት ፣ለሰላም በጋራ እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል፡፡