11ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ስልጠና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁ ተመረቁ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኅዳር 29/2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት የ11ኛ ዙር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና የወሰዱ ሰልጣኞች ተመርቀዋል፡፡ በስልጠናው የተሳተፉት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከሁሉም የሀገራችን ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ 1444 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ናቸው፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳድር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ፕሮግራሙ የወጣቱን በጎ አመለካከት የሚያዳብር እና አንዱ የሌላውን ባህልና እሴት እንዲያውቅ በማድረግ የሀገርን ፍቅር ከፍ የሚያደርግ፤ ወጣቶች በተወለዱበት አካባቢ ብቻ የታጠረ እይታ እንዳይኖራቸው የሚያደርግ እንዲሁም ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው “ወጣቶች ኃይላቸውን እና ህልማቸውን በተገቢ ሁኔታ ለበጎ ነገር ካዋሉ ለራሳቸው የሚሆን ሀገር በራሳቸው መገንባት ይችላሉ”፤ ሲሉም አክለዋል፡፡

May be an image of 2 people and daisየወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር) “ከራሳችሁ ውስጣዊ መሻት ተነስታችሁ በሀገራችን ኢትዮጵያ የቆየውን የበጎነት እሴት ተቀብላችሁ ለዚህ ታላቅ ዓላማ በመቆማችሁ ሀገርን የኮራችሁ ናችሁና እንኳን ደስ አላችሁ፤ በውስጣችሁ ያለውን አቅምና ፍላጎት አቀናጅታችሁ እርዳታ የሚፈልጉ ወገኖችን ተግታችሁ በማገልገል ለሀገር እና ለወገን ያላችሁን ፍቅር በተግባር እንድታሳዩ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

May be an image of 1 person and studyingተመራቂ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ በሁሉም ክልሎች ተሰማርተው በሚሰጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገር ግንባታው ገንቢ ሚናቸውን እንደሚወጡ ተገልጿል።