የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በተቋሙ የተከናወኑ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኮንፈረንሶች አፈፃፀምን ገምግመዋል
የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በተቋሙ የተከናወኑ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኮንፈረንሶች አፈፃፀምን ገምግመዋል
አህጉራዊ የሰላምና አለም አቀፍ ኮንፈረንሶቹ ሀገራችን በሪፎርም ስራዎች የተከናወኑ የለውጥ ስራዎች ውጤታማነትን ልምድ ያካፈለችበት ነበር።
ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በተቋሙ የተከናወኑ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኮንፈረንሶች አፈፃፀምን ገምግመዋል።
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት የተከናወኑት ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ተቋማት እና አህጉራዊ የሰላም ኮንፈረንሶች በአጠቃላይ ሰላሣ ስድስት ሀገራት መሳተፋቸውን ገልፀዋል።
በነበሩት ውይይቶች፣ የሰላምና ፀጥታ ተቋማት እንዲሁም የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጉብኝቶች፣ የሰላምና የፀጥታ ተቋማት ሪፎርም ስራዎች ውጤታማነት በተሳታፊ ሀገራት አድናቆት ሊያገኝ መቻሉንና ሀገራችን እያከናወነችው ያለው ዘርፈ ብዙ የለውጥ ስራዎች በጥሩ ልምድ መወሰዱን ጠቁመዋል።
የተለያዩ ሀገራት በአብሮነትና በሰላም ግንባታ ያሳኳቸውን ልምዶችንም ማካፈል እንደቻሉም ሚኒስቴር ዴዔታው ተናግረዋል። ስራን ከተለያዩ ተቋማት በቅንጅት መምራት መቻላችን ኮንፈረንሶቹ ውጤታማ ሆነው እንዲጠናቀቁ አስችሏልም ብለዋል።