19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተከበረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ''ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ሃሳብ 19ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አክብረዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አንዲሰፍን እና ብሔራዊ መግባባት እንዲጎለብት በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተመካክረን እና ተወያይተን የጋራ አቋም መያዝ ይኖርብናል ብለዋል።

እንደ ሀገር አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገን መስራት ይኖርብናል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴዔታው የሚታዩ ልዩነቶችን ወደጎን በመተው እና የጋራ ትርክቶች ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) አክለውም የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል መከበሩ ዓላማው ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች May be an image of 1 personያላቸውን እምቅ ባህል እና ዕሴት በመለዋወጥና በመተዋወቅ የተሻለ ሀገር እንድትገነባ በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

''ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሔራዊ አንድነት'' የሚል ሰነድ በሰላም ሚኒስቴር የመንግስታት ግንኙነት ዴስክ ኃላፊ አቶ ግርማ ቸሩ በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

May be an image of 1 person and eyeglassesለተነሱ ሃሳቦች ማጠቃለያ የሰጡት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ እኛ ኢትዮጵያውያን ብዝሃ ሃሳብ ፣ብዝሃ ማንነት ያለን ህዝቦች ነን ያሉ ሲሆን ብዝሃነትን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ አለመቻል እንደ ሀገር አንዱ ችግር መሆኑን አንስተዋል።

የብሔር ብሔረሰቦችን እና ህዝቦች ቀን ልዩነቶቻችን ከብዝሃነታችን ጋር ሳይጋጭ ኢትዮጵያዊነታችንን የምናደምቅበት ነው ብለዋል።