የሰላም ግንባታ ሥራ ውጤታማ እንዲሆን ካስፈለገ ከሁሉም ለሁሉም በሚል መንፈስ ተቋማት ሊሰሩ ይገባል ተባለ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር )፤የሰላም ሚኒስቴር ሁለተኛውን የሰላም ምክር ቤት መድረክ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ስዩም መስፍን ሰላም ሁለት ገፅታ የያዘ ቁልፍ ተግባር ነው ያሉ ሲሆን በአንድ በኩል ሰላም ልማትን ለማፋጠን፣ዴሞክራሲን ለማስፈን እና ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ የአስቻይነት ሚና የሚጫወት ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሰላም በራሱ በግብነት ተይዞ የሚከወን ራሱን የቻለ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

 

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ዜጎች ህይወታቸውንና ንብረታቸውን እያጡ የእንግልት ኑሮ እየኖሩ ይገኛሉ ያሉት ክቡር ዶ/ር ስዩም ዜጎች ከተጋረጠባቸው አደጋ መታደግ ለነገ የማይባል ፈጣን ምላሽ ይሻል ብለዋል።

የሰላም ግንባታ ሥራ ውጤታማ እንዲሆን ካስፈለገ ከሁሉም ለሁሉም በሚል መንፈስ ተቋማት ሃላፊነት ወስደው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

 

የዛሬው መድረክ የሰላም ምክር ቤቱ እስካሁን የተከናወኑ የሰላም ግንባታና ግጭትን በዘላቂነት የመፍታት ጥረቶች በትኩረት በመገምገም በቀጣይ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን ክቡር ዶ/ር ስዩም ገልፀዋል።

ለዘላቂ ሰላማችን መሠረት የሆኑት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራዎች ምቹ መደላድል ለመፍጠርና ኮሚሽኑ የተሰጠው ተልዕኮ እንዲቃና ገለልተኝነቱን የጠበቀ ድጋፍ ማድረግ የዚህን ምክር ቤት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ ''የሰላም ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀምና የጉባዔው አባላት(ተቋማት) ለአወንታዊ ሰላም ግንባታ የውልና የተናጠል ተልዕኮ'' ሰነድ አቅርበዋል።

ክቡር አቶ ታየ የሰላም ሚኒስቴር በ2015 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት፣የተገኙ ውጤቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በስፋት አቅርበዋል።

 

በመድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየታቸውን እና ጥያቄዎቻቸውን አንስተዋል።

ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም ግጭት ከተከሰተ በኋላ ከሚደረገው ርብርብ ይልቅ ግጭት ከመከሰቱ በፊት የሚሰራው የመከላከል ስራ አትራፊ ነው ያሉ ሲሆን ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ በፍጥነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች ፍትህ ማግኘት አለባቸው ያሉት ክቡር አቶ ብናልፍ ለዚህ አስተዋፅኦ የሚያደርግ የሽግግር ፍትህ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም የሰላም ምክር ቤት በቀጣይ ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ አራት ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን እነዚህም አስቀድሞ ግጭትን መከላከል ላይ፣የውይይትና የድርድር ባህል ከፍ እንዲል መስራት፣የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቦታቸው መመለስ እና አንድነታችንን የሚያጠነክሩ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።