የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም አዲስ ለተሾሙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የሥራ ርክክብ አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኅዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም አዲስ ለተሾሙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የሥራ ርክክብ እና የሰላም ሚኒስቴር እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት አስመልክቶ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩ ጌታ ገነነ፣ በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና የካውንስል አባላት ለክቡር አምባሳደር ብናልፍ ፍቅራቸውን እና አክብሮታቸውን የገለፁ ሲሆን አዲስ ለተሾሙት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል።

ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ለተደረገላቸው አሸኛኘት አመስግነው አመራርነት የተለየ ዋጋ የሚያስከፍል እና የተለየ እድል ያለው ነው ብለዋል።

ክቡር አምባሳደር ብናልፍ ከህይወት ልምድ ብዙ ተምሬያለሁ ከህይወት ፈተናዎች ብዙ ጥንካሬዎችንም አግኝቻለሁ ብለው ልምዳቸውን በሰፊው ያካፈሉ ሲሆን በተቋሙ በነበራቸው ጊዜ ብዙ ስኬት የተመዘገቡበት እና ብዙ ፈተናዎች ያለፉበት ጊዜ እንደነበር አንስተዋል።

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው ስለ ሰላም ለመስራት ዕድል በማግኝቴ ዕድለኛ ነኝ ብለዋል።

May be an image of 5 peopleበቆይታዬ ትልልቅ ሥራዎችን የምናከናውንበት እንደሚሆን አምናለሁ፣ ለክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም መልካም የስራ ዘመን እመኛለሁ ብለዋል።