የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው ለመመለስና በዘላቂነት ለማቋቋም በሚያስችል ፕሮጀክት ላይ ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን በራሳቸው ፈቃድ ተሳትፎና ፍላጎት ባረጋገጠ መልኩ ወደ ቄያቸው ለመመለስ እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግ በሚያስችል ፕሮጀክት ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡May be an image of 9 people

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚመለከታቸውን የፌዴራልና ክልል ተቋማት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ይህንን ተልዕኮውን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም እንዲያስችል የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫዎች መሠረት በማድረግ ተፈናቃዮችን የመመለስና በዘላቂነት የማቋቋም ስራውን ያከናውናል ፡፡

ፕሮጀክቱ በተለያዩ ክልሎች በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ 3.1 ሚሊዩን ዜጎች ለማስመለስ እና ለማቋቋም የተዘጋጀ ሲሆን የዚህ ፕሮጀክት አስፈላጊነት ለአገር ውስጥ ተፈናቃዩች ወሳኝ እና አስቸኳይ ሰብአዊ ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት፣ ወደ ቀያቸው ለመመለስና እና በዘላቂነት በማቋቋም በሰላም ተረጋግተው እንዲኖሩ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡