ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት 20ኛው የፓሌርሞ ኮንቬንሽን ሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ጉባኤ ተካሔደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኢ... የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም የተመራ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በፓሌርሞ ኢጣሊያ በተካሔደው 20ኛው የፓሌርሞ ኮንቬንሽን ሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ ተሳትፈዋል ፡፡

 

በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተገኙበት 20ኛው የፓሌርሞ ኮንቬንሽን የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ህገ-ወጥ ስደተኞች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሒዷል ፡፡

 

ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የስደተኞች መነሻ፣ መሸጋገሪያና መድረሻ እንደመሆኗ ህገ-ወጥ ስደትና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር እየወሰደች ያለችውን የፖሊሲ ማእቀፎች፣ ተቋማዊ አደረጃጀቶች እና የማስተካከያ እርምጃዎችን በመድረኩ አንስተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ከሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን በመድረኩ ላይ ጠቁመዋል፡፡