"የምትተክል ሀገር ፣ የሚያፀና ትውልድ" የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ተከናወነ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሐሴ 17ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ መልእክት ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

በመርሐ-ግብሩ መልእክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) "በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ጥሪ መሠረት 'የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ' በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለው የችግኝ ተከላ መርሐ -ግብር መላ ሀገራችን በአረንጓዴ ልማት በልፅጋ ለዓለም ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችላት እና ለቱርስት መዳረሻነት ተመራጭ እንድትሆን የሚያስችላት ነው" ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ "ካለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ወዲህ እየተከናወነ ያለው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ችግኝ የመትከል መርሐ-ግብር ዜጎች በሀገር ግንባታው ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ እድል የፈጠረ ነው" ብለዋል። በመርሐ-ግብሩ የሃይማኖት አባቶችም ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ ሠራተኞች ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የየካ ክፍለ ከተማ አመራሮች፣ ሠራተኞችና ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና የለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የጫካ ፕሮጀክት ልዩ ስሙ ጅፋራ በር በመገኘት አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !