ዩናይትድ አረብ ኢምሬት ለሰላም ሚኒስቴር 40 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ
ዩናይትድ አረብ ኢምሬት ለሰላም ሚኒስቴር 40 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ
ነሐሴ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ዩናይትድ አረብ ኢምሬት ለሰላም ሚኒስቴር 40 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ዩናይት አረብ ኢምሬት ከተቋማችን ጋር በመሆን የሰላም ግንባታ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ቃል በገቡት መሰረት ድጋፉን እንዳደረጉ ገልፀዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴታው አክለውም የተደረገው ድጋፍ የመኪና፣ ላፕቶፕ እና ቴምር እንደሆነ ገልፀው 40 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር ይገመታል ብለዋል። ከተበረከተው 10ቶን ቴምር 5 ቶን ቴምር በጎፋ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች፣ በተለያዩ የከተማችን ክፍሎች ለሚገኙ አረጋውያን መርጃ ማዕከሎችና ለሃይማኖት ተቋማት እንደተበረከተ አስገንዝበዋል።
የመሀመድ ቢን ዚያድ የሰብአዊነት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ክቡር ካሀሊፋ አል ዳህሊን በበኩላቸው በሰላም ሚኒስቴር በኩል የተደረገላቸውን አቀባባል አድንቀው በኢትዮጵያና በአረብ ኤምረት መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው በተለይም ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በቀጣይም ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ እና አሁን እንደመጀመሪያ የተደረገው ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡