የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት አካሄዱ
የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት አካሄዱ
ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ አረጋዊያንና ለአቅመደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ፈጽመዋል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በመርሐ-ግብሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት የመጠገንና ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አንደተደረገ ገልፀዋል፡፡ ህፃናትና ወጣቶች የሀገርን ሰላም ከመገንባት አንፃር ያላቸው ሚና የጎላ በመሆኑ በትምህርታቸው ውጤታማ በመሆን ሀገር ተረካቢ ዜጋ እንዲሆኑ ይህን ድጋፍ ልናደርግ ችለናል ብለዋል። ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም አረጋውያንም የማንነታችን መሰረቶች በመሆናቸው ዛሬ በትውልድ ቅብብሎሽ ሁሉም እዚህ እንዲደርስ የአሻራቸው ውጤት በመሆናችን የሁላችንም ኃላፊነት ናቸው ብለዋል።
ሰላም የሁላችንም ጥረት ይጠይቃል ያሉት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ እኔ የሰላም ባለቤት ነኝ በማለት ሁላችንም ለሰላማችን ዘብ ልንቆም ይገባል ብለዋል። የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በከተማችን በመገኘት ኢትዮጵያዊነትን የሚያፀና የበጎነት ተግባር በመፈፀማቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለምን ጨምሮ፣ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በመርሐ-ግብሩ ተሳትፈዋል፡፡