የብሄራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ላይ መሳተፍ ከዕድለኝነት ባሻገር የህሌናና የመንፋስ እርካታ የሚሰጥ ተግባር ነው፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

"የብሄራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ላይ መሳተፍ ከዕድለኝነት ባሻገር የህሌናና የመንፋስ እርካታ የሚሰጥ ተግባር ነው፡፡"

አቶ ገመቺስ እትቻ

ዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ለአምስተኛ ዙር "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሀሳብ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኝ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁና የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል ፡፡

በ5ተኛው ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ 10 ሺህ በላይ ወጣቶች ስልጠናቸውን የሚከታተሉ ሲሆን በዛሬው ዕለት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ 2 ሺህ ሰልጣኞች በሐይማኖት አባቶች እና በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በሰላም ሚኒስትር የብሄራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ገመቺስ እትቻ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት መርሃ-ግብር ኢትዩጵያዊ እሴቶችንና መርሆዎችን ለወጣቱ ትውልድ በማስተላለፍ በዘር፣ በጎሳ፣ በሀይማኖትና በሌሎችም ማንነቶች የወጣቶችን የሀገር እና የህዝቡን ፍቅር ለማሳደግ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል ተከስቶ የነበረው ጦርነት ኢትዮጵያ በምትፈልገው መልኩ ውሳኔ ላይ በደረሰበትና እንደ ሀገር ባሸነፍንበት ማግስት በመሆኑና የስልጠና ይዘቱም ወቅቱን የሚፈልገውን የስነምግባርና የአካል ብቃት ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ስለሆነም በሀገር ግንባታ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ መፍጠርና የወጣቶችን መልካም አስተሳሰብ ማሳደግን ያማከለ ነው፡፡

አቶ ገመችስ አክለውም የብሄራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ላይ መሳተፍ ከዕድለኝነት ባሻገር የህሌናና የመንፋስ እርካታ የሚሰጥ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ የዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት ስራ ውስጥ የራሳችሁን አወንታዊ አሻራ በማሳረፍ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የዋቸሞ ዩንቨርሲቲ የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኑሪ ለፌቦ በበኩላቸው በጎ ፈቃደኝነት ያለምንም ግፊት በራስ ሙሉ ፍላጎትና ተነሳሽነት የሚሰራ መልካም ስራ ሲሆን የበጎ ፈቃድ ተግባር የህሌናን ፈቃድ ተከትሎ የሚፈጸም የፍቅር ተግባር ሆኖ መንፈሳዊ እርካታ የሚሰጥና አንዱ ያለውን ማንኛውንም ነገር በፍቅር ለሌሎች በመስጠትና በማካፈል ፣ ያለውን በአግባቡ በመጠቀም ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማሳደግ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ስለሆነም በዩንቨርሲቲ ቆይታችሁ ለአገልግሎት ስንቅ የሚሆነውን ስነ-ምግባርን ፣የአመለካከትና ክህሎትን ይዛችሁ ለመውጣት በጥብቅ ዲስፕሊን እንድትከታተሉ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡