ዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ለአምስተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኝ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ለአምስተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኝ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁና የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡

በፕሮራሙ በሰላም ሚኒስቴር በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትር ዋና አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ እንደተናገሩት በጎ ፈቃደኝነት ያለ ማንም ግፊት በራስ ተነሳሽነት የሚፈፀም የህሊና እርካታ የሚሰጥ ተግባር መሆኑን ገልፀው "በጎነት ለአብሮነት" በሚል የተዘጋጀው መርሃግብር አንዱ የሌላውን እሴት እንዲያውቅና እርስ በእርስ በመጋመድ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚያግዝ ፕሮግራም ነው በማለት ገልፀዋል፡፡

አቶ ካይዳኪ አክለውም በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ የሆናችሁ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ያለውን መከፋፈልና ጥርጣሬ በማስወገድ ሃገራዊ አንድነትን ለማጠናከር የጎላ ሚና ያላችሁ በመሆኑ የሚሰጠውን ስልጠና በብቃትና ስነምግባር በተሞላው መልኩ በመከታተል ይህን ሀገራዊ ሃላፊታችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ በበኩላቸው የሰላም ሚኒስቴር ወጣቶች ላይ እየሰራ ያለው ሥራ ወቅቱን የጠበቀና ጊዜውን የሚመጥን መሆኑን ገልፀው ዩኒቨርሲቲው ለወጣቶች የሚያስፈልገውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ያለው ዝግጁነት ገልጸዋል።

በአምስተኛው ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም በአምስት ዩኒቨርስቲዎች ከ10ሺህ በላይ ወጣቶች ስልጠናቸውን የሚከታተሉ ሲሆን በዛሬው ዕለት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ 1000 ሺህ ሰልጣኞች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።