የዓድዋን ድል ታላቅነት ለሰላም

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስከበርና የህዝቦቿን አንድነት ለማስጠበቅ በተለያዩ የዘመን አጋጣሚዎች ወረራ የፈፀሙባትን የውጪ ወራሪ ኃይሎች በመፋለም በበርካታ አውደ ውጊያዎች ላይ ተደጋጋሚ የሆኑ ሀገርን ያፀኑና ያስቀጠሉ ታሪካዊ ድሎችን ተጎናፅፋለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው የሀገራችን ብቻ ሣይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች ድል የሆነው የዓድዋ ድል ነው፡፡ ከዛሬ 129 ዓመታት በፊት አያቶቻችን ባርነትንና ቅኝ ግዛትን እምቢ ብለው የቋንቋ፤ የኃይማኖት፣ የፆታና የባህል ልዩነት ሳይበግራቸው ወራሪውን የጣሊያን ሠራዊት በዓድዋ ምድር በፍፁም ጀግንነትና በሀገር ፍቅር ስሜት ተፋልመው ድል በማድረግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አስከብረዋል፡፡ ሀገርና ሀገረ-መንግሥት አስቀጥለዋል፡፡

የዚህ ባለታሪክ ትውልድ ልጆች የሆንነው እኛ ኢትዮጵያዊያን የቀደምቶቻችን ፈለግ ተከትለን ለሀገር ሉዓላዊነትና ለግዛት አንድነት የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን ውለታ በማሰብ የኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ሰላም እና አብሮነት ማስጠበቅ እና ልማትን እውን ማድረግ መቻል ነው፡፡ ዛሬ ላይ በተለያዩ ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ምክንያቶች በሰላም መደፍረስ እየተፈተነች ላለች ሀገራችን እና ሰላምን ለሚሻው ሕዝባችን ሁላችንም የሰላም አምባሳደር በመሆን ልንቆም ይገባል፡፡

የግጭት እና ያለመግባባት ታሪካችን ተዘግቶ በጋራ ታሪኮቻችን እና በጋራ ማንነቶቻችን ላይ የምንግባባ፤ ለጋራ ሀገራችን ሌት ተዕቀን የምንተጋ፤ ለልጆቻችንም የበለጸገችና ሰላሟ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለማውረስ የጋራ እሳቤ ያለን የለውጥ ትውልድ መሆን ይኖርብናል፡፡

እኛ ኢትዮጵያዊያን የሀገራችንን ዳርድንበርና ሉዓላዊነት ከመጠበቅ ጎን ለጎን ዘላቂ ሰላማችንን እና ብሔራዊ መግባባትን ከፍ በሚያደርጉ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የማያግባቡን አጀንዳዎች ሲገጥሙን ደግሞ ቁጭ ብሎ በመመካከር እና በመወያየት ልንፈታ ይገባል፡፡ በሰላም እና በልማቱም መስክ ሀገራችንን ወደ ፊት ሊያራምዱ የሚያስችሉ ተግባራትን በመፈጸም ነጻነቷን ምሉዕ አድርገን ልክ እንደቀምት አባቶቻችን የዓድዋ ታሪክ የሚዘከር የራሳችን አኩሪ ታሪክ ሊኖረን ይገባል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ!