በዓድዋ እሴቶች እየተገነባን የሀገራችንን ሰላም እናረጋግጣለን!!

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን ዘመን ተሻጋሪ ግዙፍ የነጻነት አርማ ነው፡፡ የዓድዋ ድል የሰው ልጆች ለነጻነት የከፈሉት መስዋዕትነት ሕያዉ ማሳያ ምልክትም ነው፡፡ ይህ ግዙፍ የነጻነት ታሪክ የዓለምን የቅኝ ግዛት እሳቤና ተግባር የሰበረ፤ የፀረ ቅኝ ግዛት ትግል አቅጣጫን ያመላከተ እና የታሪክ ብያኔን ከመሠረቱ የቀየረ ነው፡፡

የዓድዋ ድል ሉዓላዊነታችንን ያስከበርንበት፤ ወራሪ ጠላትን ያሳፈርንበት ታላቅ ድል በመሆኑ እየዘከርንና ታሪኩን በልኩ እያወሳን ለቀጣይ ትውልድ የማሻገር ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ታላቅ ድል እያንዳዳችን ልንማርባቸውና የዘወትር አስተሳሰብ ሊያደርጋቸው የሚገቡ በርካታ እሴቶች እንዳሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

የዓላማ ፅናት፣ አንድነት፣ የመሪ ትዕዛዝ ማክበር ፣ ሃገርን ማስቀደም፣ ምክኒያት ያለማብዛት፣ የሀገር ፍቅርን ፣የመንፈስ ጥንካሬ፣ ጽናት እና የአልሸነፍ ባይነት ወኔን በዚህ ዘመን ያለን ኢትዮጵያዊያን ለንማር ይገባል፡፡

እኛ የዚህ ዘመን ትውልዶች የዓድዋን ድል በዓል ስንዘክርና ስናከብር የኛ ዘመን አድዋ ምን መሆን አለበት? ምንስ ማድረግ አለብን? የሚለው አንኳር ጥያቄ ምላሽ የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከቀደሙት ጀግኖች አያቶቻችን የተረከብናትን ሉዓላዊት ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጪ የሚቃጡባትን ትንኮሳዎች እየመከትንና ጠላቶቿን እየደመሰስን ሁለንተናዊ ሰላሟ የተረጋገጠ፣ አንድነቷ የተጠበቀና የፀናች ኢትዮጵያን ለትውልድ የማሻገር ግዴታ አለብን፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ!