Asset Publisher

null የሰላም ሚኒስቴር ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ

ሐምሌ 5/2017ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) ፤ የሰላም ሚኒስቴር በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

መድረኩን የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የዛሬው መድረክ በ2017 በጀት ዓመት ተቋማችን ያከናወናቸውን ተግባራት በጥልቀት በመመልከት የተገኙ መልካም ውጤቶችን ለማጠናከር እና ያጋጠሙ ችግሮችን ደግሞ በመፍታት በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ሥራ ለመስራት ያለመ ነው ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡት የሰላም ሚኒስትር አማካሪ እና የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ሰውነት ቸኮል የሰላም ሚኒስቴር በ2017 በጀት ዓመት በአወንታዊ ሰላም ግንባታ፣ በሀገር ግንባታ፣ በሰላም የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ፕሮግራም፣ በግጭት መከላከልና አስተዳደር፣ በፌዴራሊዝምና የመንግስታት ግንኙነት እንዲሁም በተቋማዊ ሪፎርምና የማስፈፀም አቅምን ለማሳደግ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የተገኙ ስኬቶችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

አቶ ሰውንት ቸኮል የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን ያቀረቡ ሲሆን የዘንድሮ ዕቅድ በየደረጃው ካሉ አመራሮችና እና ሰራተኛች ሰፊ ውይይት ተደርጎበት የታቀደ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በጀት ዓመት የሚከናወኑ አንኳር ተግባራት ተለይተዋል ብለዋል።

ያሉ ሀገራዊ ዕድሎች እና ስጋቶች በዕቅዱ ውስጥ በጥልቀት ታይተዋል ያሉት አቶ ሰውነት በጀት ዓመት ህዝብን በስፋት የሚያሳትፋ ትልልቅ ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የሰላም የንቅናቄ ሥራዎች ለማከናወን ታቅዷል ብለዋል።

በቀረበው ሪፖርት እና ዕቅድ ከሰራተኞች አስተያየትና ጥያቄ ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል፡፡