የሰላም ሚኒስቴር ኢምፓቲ ፎር ላይፍ ኢንተግሬትድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን/ELIDA/ ከተሰኘ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት አካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ኢምፓቲ ፎር ላይፍ ኢንተግሬትድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን /Empathy For Life Integrated Development Association/ ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በሴቶች የሰላም ግንባታ ሚና ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት አካሂደዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በስምምነቱ ላይ እንደተናገሩት በአወንታዊ የሰላም ግንባታ ሂደት ላይ የሴቶች ሚና የማይተካ መሆኑን ገልፀው የሰላም ሚኒስቴር ሴቶች በሰላም ግንባታና በግጭት አፈታት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከፍ የሚያደርጉ ሥራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የሚካሄዱ የሰላም ግንባታ እና የግጭት አፈታት ሂደቶች ሴቶችን ያካተተ መሆን ይኖርበታል ያሉት ክቡር ዶ/ር ከይረዲን የሴቶችን አቅም ማሳደግም ሌላው ሊተኮርበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ኢምፓቲ ፎር ላይፍ ኢንተግሬትድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን /Empathy For Life Integrated Development Association/ ኮፋውንደር ዚነት ይመር በበኩላቸው ድርጅታቸው የሴቶችንና ወጣቶች አቅም ለማሳደግ የተቋቋመ መሆኑን ገልፀው ሴቶች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና እንዲወጡ በቀጣይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡