የሰላም ሚኒስቴር ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ጋር በሰላም ግንባታ ላይ ለመስራት የሚያስችለውን የ1.8 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት ስምምነት አካሂዷል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ለወርልድ ቪዥን ኢትዮጵ ኃላፊዎች የሰላም ሚኒስቴር እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት እና መሰረታዊ የሀገር መንግስት ግንባታ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የንቅናቄ ስራዎች አስመልክቶ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ አክለውም የሰላም ሚኒስቴር የዘላቂ ሰላም ስራዎችን እና የብሔራዊ መግባባት ተግባራትን ለማጎልበት በሰላም ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን የዛሬው ስምምነትም የዚሁ አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡

የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሪክተር ካርሜን ቲሊ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ አመስግነው በሰላም ላይ መስራት ራስ ላይ መስራት እንደመሆኑ መጠን በሰላም ግንባታ ላይ ለመስራት ዕድሉን በማግኘታችን ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡