በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የሰላም ስምምነት ተካሄደ
በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የሰላም ስምምነት ተካሄደ
በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሰላም ስምምነት መፈራረሙ ለሀገራችን ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የተካሄደው የሰላም ስምምነት እጅግ የሚደነቅ ነው። ሂደቱ የሰላም መንገድ ብቸኛ መንገድ መሆኑ ግንዛቤ የተፈጠረበት ነው።
ይህ እንዲሳካ የኦሮሚያ ክልል መንግስት መላው የኦሮሞ ህዝብ በተደጋጋሚ ላደረገው ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰላም ጥሪ ተገቢ ምላሽ በመስጠትና በመቀበል የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሆኑት ጃል ሰኚ ነጋሳ ያደረጉት የሰላም ስምምነት በሀገራችን ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም መረጋገጥ አበርክቶ ያለው በመሆኑ ሚኒስቴር መ/ቤታችን በአድናቆት የሚመለከተው ሲሆን ፤ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ልዩነቶች በዘመናዊ መንገድ በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረጉ መሰል ጥረቶች ሁሉ እንዲሳኩ የሰላም ሚኒስቴር የበኩሉን ሚና የሚጫወት ይሆናል። ለመላው የሀገራችን ህዝቦች በአጠቃላይና ለኦሮሞ ህዝብ በተለይ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያ!
የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር