አዎንታዊ ሰላም

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒቴር አዎንታዊ ሰላም ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብ እና ለማሳደግ፤ ግለሰብ፣ ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ አዎንታዊ ሰላም ለመገንባት ሁሉንም በየደረጃው የሚገኙ አካላትን በስፋት በማሳተፍ እና በባለቤትነት መንፈስ እንዲሰሩ የሚያስችሉ አደረጃጀቶችን፣ አሰራሮችን እና ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በሀገራችን አዎንታዊላም በግለሰብ፣ በቤተሰብና በማህበረሰብ ደረጃ መጠበቅ፣ መንከባከብ እና ማሳደግ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

ተቋማችን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በግለሰብ፣ በቤተሰብ እንዲሁም በማህበረሰብ ደረጃ የሚከሰቱ የስነ ልቦና እና አካላዊ ጥቃት፣ የሰላም እጦቶች፣ የጽንፈኝነት ስጋቶች፣ የመጤ ባህሎችና ልማዶች የሚያደርሱትን አሉታዊ ተጽኖ አስቀድሞ በጥናት በመለየት ችግሮችን ከመሰረታቸው ለመፍታት የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት እየተከተለ ይገኛል፡፡

አዎንታዊ ሰላም መጠበቅ፣ መንከባከብና ማሳደግ ስራዎች ላይ ክትትል በማድረግ ያሉትን ችግሮችና ክፍተቶች ለመቅረፍ የሚያስችሉ የፖሊሲ፣ ስትራቴጂ አሊያም ደግሞ ህጋዊ ማዕቀፍ በማዘጋጀት እንዲሁም በአሰራርና አደረጃጀታቸው ላይ የሚስተዋሉ ድክመቶችን መቅረፍ ያስፈልጋል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ!