የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሰላም ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ ተረከበች

Kapslade applikationer

Innehållspublicerare

null የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ ተረከበች

ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ ተረክባለች።

ቦታውን አሜሪካ የሚገኘው የኋለኛው ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን (Church of Jesus Christ of Latter-day Saints (LDS),) ያበረከተ ሲሆን የስተርሊንግ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ተብሏል።

May be an image of 4 people, dais and textየሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በርክክብ ስነ ስርዓት ወቅት እንደተናገሩት የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት ለስራ በሄድንበት ወቅት በግዛቱ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አምነት ተከታይ ምዕመናን የማምለኪያ ቦታ የሚሆን ቤተክርስቲያን ባለማግኘታቸው ሲቸገሩ ማስተዋለቸውን ገልፀው ችግሩን ለመፍታት የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በጋራ ባደረጉት ጥረት ቦታው እንዲገኝ ሆኗል ብለዋል።

መንግስት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅርርብ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ምዕመናን ሃይማኖታቸውን በነፃነት እንዲያራምዱ እና በሃይማኖቶች መካከል የአብሮነት እና የትብብር መንፈስ እንዲያድግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

May be an image of 6 people, dais and the Oval Officeየኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን (Church of Jesus Christ of Latter-day Saints (LDS),) የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታውን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማስረከቡ በሐይማኖቶች መካከል ያለውን የመደጋገፍ ፣የአብሮነት እና የትብብር መንፈስ ያሳያል ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ዕሴት ሆኖ ለዘመናት ቆይቷል ብለዋል።

መንግስት ዜጋ ተኮር የሆነ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሚኒስትር ዴዔታው ከዚህ የወሰድነው ትምህርት አንዱ ሃይማኖት አንዱን መደገፍ ከቻለ እና በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መተባበር ከቻሉ ሀገር ሰላሟ እንደሚፀና ነው ብለዋል።

May be an image of 6 people and textየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ በማግኘቷ ታላቅ ደስታ ይሰማናል ፣በሂደቱ ድጋፍ እና ትብብር ለአደረጉ ሁሉ ምስጋናዬ ላቅ ያለነው ብለዋል።

Innehållspublicerare

የክቡር የሚኒስትሩ መልዕክት

አቶ መሐመድ እድሪስ መሐመድ የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስትር

የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባራት መካከል ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ የፌዴራል ሥርዓቱ የግንኙነት ማዕከል ሆኖ ማገልገል፣ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከልና ማስተዳደር ሲሆን እነዚህን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያከናውናል።

ተጨማሪ

Kapslade applikationer

Innehållspublicerare

ትንታኔ

በዓድዋ እሴቶች እየተገነባን የሀገራችንን ሰላም እናረጋግጣለን!!

የዓድዋ ድል ሉዓላዊነታችንን ያስከበርንበት፤ ወራሪ ጠላትን ያሳፈርንበት ታላቅ ድል በመሆኑ እየዘከርንና ታሪኩን በልኩ እያወሳን ለቀጣይ ትውልድ የማሻገር ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ታላቅ ድል እያንዳዳችን ልንማርባቸውና የዘወትር አስተሳሰብ ሊያደርጋቸው የሚገቡ በርካታ እሴቶች እንዳሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

Innehållspublicerare

ቪዲዮ ዜና

የሰላም መንገድ
በጎነት ለአብሮነት
በጎነት ለአብሮነት
final The Vanguard of Peace