የሀገረ ብሔር ግንባታ/ Nation Building ምንነት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሀገረ ብሔር ግንባታ/Nation Building/ ስንል በአንድ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች የጋራ ማንነታቸውን፣ የጋራ አመለካከታቸውን ፣ እምነታቸውንና የጋራ እሴታቸውን የሚገነቡበትና የሚያዳብሩበት ሂደት ነው፡፡ ይህም በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ካለፈው ታሪካቸው እና ከአሁኑ የጋራ አኗኗራቸው የመነጨ የጋራ አመለካከት እሴቶችና እምነቶች የሚገነቡበት እና ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትና ህዝቦች የሚለያቸው የጋራ መለያ ባለቤት የሚሆኑበት ሂደት ነው፡፡

ይህን አብሮ የመኖር ታሪክ በዘመናዊ ትምህርት ተደራሽነት፣ የሕዝቦችን መስተጋብርና የኢኮኖሚ ውህደት ለማሳለጥ የሚያስችል የመስረተ ልማት ዝርጋታ፣ የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ግንባታ እያደገና የሕዝቦች ትስስር (የአንዱ ልማት ለሌላው ጸጋ፤ የአንዱ ጉዳት ለሌላውም አደጋ መሆኑ) በተጨባጭ የሀገረ-ብሔር ግንባታ /Nation Building/ እንዲሳካ እንዲሁም ይህንን ሂደት የማፅናት ስራ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ይሆናል፡፡

በመሆኑም ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መሰረት የሚሆኑ ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትሕ እና ለህግ-ተገዥነት (Rule of Law) በማጎልበት ዴሞክራሲ የሰፈነባት ጠንካራ አገር ለመገንባት ያገኘነውን አገራዊ የለውጥ ዕድል በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

በጥቅሉ ብዝኃነት በሰፈነበት አገር ሀገረ ብሔር ግንባታ/Nation Building ከባድ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት በዘመናት ጥረት የሚገነባ ነው፡፡ ሀገር ብሔር ግንባታ ተፃራሪ የሆኑ ለአንድነት የማይበጁ አስተሳሰቦችንና ተግባራትን በጥብቅ ከማረምና ከማስተካከል ጋር የተያያዙ ከባድ ጥረቶችን በማካሄድ የጋራ ፍላጎት፣ ዕድገትና ብልጽግናን በማለም ሊሳካ የሚችል ግን ከባድና ትልቁ የቤት ስራ ነው፡፡

ሀገራችን ለሁላችንም ትበቃለች፣ የሚል ጽኑ ሐሳብ በመያዝና የዕጦት አስተሳሰብን በመሻገር ለሁሉም ዜጎች የምትሆንና ሁሉም በኩራትና በምቾት የሚኖርባት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሁሉም ህብረተሰብ ትግልና ተሳትፎ ያስፈልጋል::

ሰላም ለኢትዮጵያ !