Publicador de Conteúdos e Mídias

Conteúdos Mais Vistos

null የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሞሮኮ ኢምባሲ ጋር በሁለቱ ሀገራት የሰላም አጀንዳዎች ዙሪያ ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄደ

ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሞሮኮ ኢምባሲ ጋር በሁለቱ ሀገራት የሰላም አጀንዳዎች ዙሪያ ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል፡፡

በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዛ አላኦኢ መሐምዲ እና ከሞሮኮ የመጡ ልዑካን ቡድን በውይይቱ የተገኙ ሲሆን የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት  ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የሁለቱን ሀገራት ጥቅምና መብት ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ልምድንና እውቀትን በማቀናጀት ለሰላም ግንባታ ስራዎች ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት መሆኑን ገልፀዋል።