Publicador de Conteúdos e Mídias

null ሀገራዊ የግጭት ክስተቶች ፣መንስኤዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች "ላይ የተካሄደ ጥናት ውጤት ይፋ ተደረገ

ኅዳር 23/2016 . (የሰላም ሚኒስቴር)፣ "ሀገራዊ የግጭት ክስተቶች ፣መንስኤዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች "ላይ የተካሄደ ጥናት ውጤት ይፋ የማድረግ መርሃ -ግብር ተካሄዷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ በሀገራችን 2010 . እስከ 2015 . ድረስ በተለያዩ ክልሎች በተለያዩ ምክንያቶችና የግጭት መንስኤዎች የሚከሰቱ ግጭቶች ወደ ሁከትን እና ብጥብጥ አድገው ከፍተኛ ጉዳት በሰውና በንብረት ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ እያደረሱም ነው ብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር እነዚህ የሚስተዋሉ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን ለመፍታት በተናጠል ከመስራት ማህበረሰባዊ ለውጥ ሊያመጣ በሚያስችል መንገድ ሁሉንም ዜጎችና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ጥናቶችን ሲያካሂድ ቆይቷል በማለት ክቡር ሚኒስትር ደኤታው ገልፀዋል  ፡፡

አክለውም በዛሬው ዕለት ይፋ የሚደረገው ጥናት ዋና ዓላማ እና አስፈላጊነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ግጭቶች መንስዔዎቻቸውን በመለየት፤ በቴክኖሎጂ የታገዘ የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ስርዓትን በመዘርጋት ግጭቶችን ከመከሰታቸው በፊት መከላከል፣የህብረተሰቡን በሰላም የመኖር ልምድ በመጠቀም እና የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት የዘላቂ መፍትሄ አማራጮችን መጠቆም ነው ብለዋል ፡፡

''ሀገራዊ የግጭት ክስተቶች ፣መንስኤዎችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች'' በሚል ርዕስ ጥናት ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጰያ ጥናትና ምርምር ተቋም ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የምርምር  ክፍል ኃላፊ የሆኑት / ደሳለኝ አምሳሉ  ናቸው።

/ ደሳለኝ በጥናታቸው በኢትዮጵያ (2018-2022 ..) የተከሰቱ ግጭቶች መንስኤዎችና የመፍትሄ ሃሳቦችን በዝርዝር  አስቀምጠዋል።

ጥናቱ በኢትዮጵያ የተነሱ ግጭቶች በየትኞቹ የሀገራችን ክፍሎች በብዛት ተስተዋል የሚለውን የሚያሳይ የግጭት ፍኖተ ካርታ/conflict mapping/ የያዘ ሲሆን የተከሰቱ ግጭቶች መሰረታዊ እና አባባሽ ምክንያቶችን እና ምን ቢደረግ ግጭቶች ሊቀንሱ ይችላሉ ሚለውን ሃሳብ አስቀምጧል።

በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር / ስዩም መስፍን የሰላም ሚኒስቴር በተሰጠው ስልጣን መሰረት ግጭቶች መንስኤዎችን አጥንቶ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በጥናት ለይቶ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ ገልፀው ዛሬ ይፋ የተደረገው ጥናት ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት በጋር በመሆን የተካሄደ እንደሆነ እና ከትግራይ ክልል በስተቀር ጥናቱ ሁሉንም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ያካተተ መሆንንአስገንዝበዋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰላምና የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና የኮሚቴ አባላት ፣የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ፣የፌዴራልና የክልል የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች እና የባለድርሻ አካላት አመራሮች በፕሮግራሙ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡