ኢትዮጵያዊ በጎ እሴቶችና ዓለም አቀፋዊነት
ኢትዮጵያዊ በጎ እሴቶችና ዓለም አቀፋዊነት
ሀገራዊ እሴቶቻችን የማንነታችን መሠረት ናቸው፡፡ በኢትዮጵያዊነታችን በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ በመረዳዳት፣ በመደጋገፍና በመተሳሰብ የተመሠረተ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን፤ ብሎም በሕዝቦች መካከል ዘላቂ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲፈጠር በማድረግ እሴቶቻችን ሚናቸው ጉልህ ነው፡፡
እነዚህ መልካም እሴቶች በተለያዩ ሁኔታዎችና ምክንያቶች የሚፈጠሩ ችግሮችን በመፍታት፣ አለመግባባቶችን በማስቀረት፣ እንደ ሀገርም የገጠሙንን ፈተናዎች አልፈን የጋራ ታሪካችንን እንድናዲስ የሚያግዙን ማኅበራዊ ሃብት መሆናቸው እሙን ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን እንዲጠናከር በማድረግም በኩል በርካታ ገንቢ የሆኑ አንድምታዎች አሏቸው፡፡
እሴቶቻችን ለሰላማችን መረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ናቸው፡፡ ሀገራዊ መልካም እሴቶች እንዳይደበዝዙ ብንጠብቅ ሰላማችንን እና የሁላችንም መገለጫ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን እንድንጠብቅ ይረዳናል፡፡ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ የጋራ እሴቶቻችን ጎልተው እንዲወጡ ማድረግ፤ እነሱን ጥቅም ላይ እያዋሉ የሚፈጠሩትን ችግሮች መፍታት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡
የራሳችን የሆኑ መልካም እሴቶችን ለሰላም ግንባታ ልንጠቀም፤ በሌሎች መጤ የሆኑ አጥፊ ልማዶች እንዳይሸረሸሩ ልንጠብቅ፤ ጠብቀንም ለትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያ !