ሰላም
ሰላም
ሰላም በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብና በተቋማት መካከል፤ ከዚህም አልፎ ሀገራትን እና አህጉራትን የሚያካትት መልካም ግንኙነትን፣ አብሮነትን፣ እኩልነትን፣ ፍትሃዊነትን፣ ነጻነትን፣ በወንድማማችነትና እህትማማችነት አብሮ መኖርን በብርቱ የሚጠይቅ ነው፡፡
ባለፉት ጊዜያት በሀገራችን ላይ የታዩት የሰላም እጦት ችግሮች አብዛኞቹ በተሳሳቱ ትርክቶች ምክንያት የተፈጠሩ ናቸው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ የመጡ፤ ለረጅም ዘመናት አብረውን የኖሩትን ኢትዮጵያዊ የሆኑ መልካም እሴቶቻችን በአግባቡ ባለመረዳት፤ ባለማክበር፤ እንዲሁም ከተለያዩ የሐሰት ትርክቶች የመነጩ ናቸው፡፡
በሀገራችን በአሁኑ ጊዜ እየታየ ያለው አንጻራዊ ሰላም ይበልጥ እየተሻሻለ እንዲቀጥል እና ሀገራችን በሁሉም ዘርፎች እያደገች ወደፊት እንድትራመድ የተገኘው አንፃራ ሰላም ዘላቂ እንዲሆን ለሰላም ግንባታ ሥራው ሁሉም አስተዋፅኦ ሊያበረክትና በአብሮነት ሊቆም ይገባል፡፡
እየተሠሩ ያሉት የዘላቂ ሰላም ግንባታ ሥራዎች የሀገራችንን ታሪክ መሠረት ያደረገና የተለያዩ ሀገራትን ልምዶች ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ በመሥራት አዎንታዊ ሰላም ለማምጣት ስለሆነ በየደረጃው ማኅበረሰቦችን፣ ተቋማትን እና አጋር አካላትን በስፋት የሚያሳትፉ ናቸው፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያ !