ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ግጭት የማይጣጣሙ ግቦችና ድርጊቶች ባሏቸው ግለሰቦች ወይም ቡድኖች መካከል የሚፈጠሩ የተለያዩ ስሜቶችና ፍላጎቶችን በአሸናፊነት ለመወጣት የሚደረግ ማህበራዊ እውነታ ነው፡፡ ግጭት ድንገት ሳይታሰብ የሚመጣ ክስተት ሳይሆን በጥቅም፣ በእምነት፣ ወዘተ...ልዩነት ምክንያት የሚከሰት አለመግባባት ነው፡፡

የሚከሰቱ ችግሮችም ከማደጋቸውና በማህበረሰቡ ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ከማድረሳቸው በፊት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችሉ በብዙዎች ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው ባህላዊ የሽምግልና ግጭት አፈታት ሥርዓቶች ደግሞ በአገራችን ኢትዮጵያ በስፋት ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎችና ሌሎችም ማህበራዊ መሰረት ያላቸው የግጭት መፍቻ ስልቶች የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች እንዲጎለብቱ ገንቢ ሚና ተጫውተዋል።

እነዚህን ባህላዊ እሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እደሚችልም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ባሳለፍናቸው አገራዊ ክስተቶች ላይ የተመለከትናቸው ሲሆን ወጣቶችን የመገሰፅ እና የመምከር፣ አለፍ ሲልም በዳይን የመቅጣትና ተበዳይን የመካስ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች ምስክር ናቸው፡፡ እንዚህ እሴቶች አወንታዊ ሚናቸውን በማጠናከርና ለተተኪው ትውልድ በማሸጋገር መስራት ይኖርባቸዋል።

የሰላም ሚኒስቴርም ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓትን በማዳበር ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ እንዲያስችል ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሀይማኖት አባቶች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !