“ኅብረ ብሔራዊነት ለሰላም''

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

እኛ ኢትዮጵያውያን የአብሮነት እና የመቻቻል እሴቶች ያሉን፣ ረጅም ዘመናትን በአብሮነት ያሳለፍን፣ በጋራ ተጋድሎአችን አኩሪ ታሪክ ያስመዘገብን፣ ያጋጠሙንን ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች በጋራ የመከትን እና በህብረት የኖርን ህዝቦች ነን።

ከፍተኛ የባህል፣ የወግና ልማድ ውህደትና ጠንካራ ትስስር ያለን ህዝቦችም ነን። በጋብቻና በልዩ ልዩ የደምና ስጋ ትስስር በተገነቡ የአብሮነት እሴቶች የተጋመድን መሆናችንንም ማንም የሚረዳው እውነታ ነው።

ህብረብሔራዊነት ከብዝሃነት ውስጥ የሚወለድ የመከባበር፣ የመቻቻል፣ የመተሳሰብ፣ የወንድማማችነት እና የአብሮነት ቀለም ነው።

ኢትዮጵያ የደመቀችው፣ ያማረችው ከብዙሃነት ውስጥ በተወጣጡ ባህሎች፣ ወጎች፣ ሥርዓቶች፣ ልማዶች፣ ቋንቋዎችና ማንነቶች ነው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ቢጎል ኢትዮጵያዊነት ይደበዝዛል።

ህብረብሄራዊነት ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ እና ለብሔራዊ መግባባት መጎልበት ያለው ሚና ከፍተኛ ነው። ህብረ ብሄራዊነት ለሚገጥሙን የውስጥና የውጪ ፈተናዎች ሁሉ የመፍትሄ መንገድ ነው!!

በኅብረት ስንቆም ለዘላቂ ሰላማችን እና ለአገር አንድነት ጠንቅ የሆኑ ጉዳዮች ሲደርሱብን ለመመከት አቅም እናገኛለን፤ የሚያጋጥሙንን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ እና በዘላቂነት ለመፍታት ጉልበት ይኖረናል።

ስለሆነም የሚከሰቱ ፈተናዎች በመመከት ሀገራችንን ከነሙሉ ክብሯ ለቀጣይ ትውልድ የማሻገር ኃላፊነት እንዳለብን በመረዳት ተግተን ልንሰራ ይገባል።

የሰላም ሚኒስቴር እነዚህን “ኅብረ ብሔራዊ ሀሳቦች ይበልጥ ጎልተው እንዲወጡ እና በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት፣ በግለሰቦችና በቡድኖች መካከል የሠላም የመከባበርና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የግንዛቤና የንቅናቄ ስልቶችን በመቀየስ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !