የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር ክቡር ሞሐመድ ሳሌም አል-ራሽዲን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

Beágyazott alkalmazások

Tartalom megjelenítő

Tartalom megjelenítő

የክቡር የሚኒስትሩ መልዕክት

አቶ መሐመድ እድሪስ መሐመድ የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስትር

የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባራት መካከል ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ የፌዴራል ሥርዓቱ የግንኙነት ማዕከል ሆኖ ማገልገል፣ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከልና ማስተዳደር ሲሆን እነዚህን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያከናውናል።

ተጨማሪ

Beágyazott alkalmazások

Tartalom megjelenítő

ትንታኔ

አሰባሳቢ ትርክት ለብሔራዊ መግባባት

አፍራሽ ትርክቶች በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ጎታች አስተሳሰቦችን ከማስረፅ በተጨማሪ ለምናስባቸው ግለሰባዊ፣ ማኅበረሰባዊና ሀገራዊ ግቦች ስኬትን ሳይሆን ውድቀትን ያመጣሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ

የሰላም እሳቤ እና አስፈላጊነት

መዋቅራዊ የሰላም ግንባታ ጅምሮችን የሚያጎለብት፣ ማኅበረሰባዊ እሴቶችን ያማከለ፣ እና ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያካትት ሰላምን ይበልጥ የሚያፀና ሥራ መሥራት ከሀገራችን ተሻግሮ ለቀጣናው ሁለንተናዊ ለውጦች ፋይዳው የላቀ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ

Tartalom megjelenítő

null የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር ክቡር ሞሐመድ ሳሌም አል-ራሽዲን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

መስከረም 20/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፤ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር ክቡር ሞሐመድ ሳሌም አል-ራሽዲን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት በማድነቅ የሰላም ሚኒስቴር በሰላም ግንባታ፣ሰላምን በሚያጠናክሩ እና በሚያጸኑ የተለያዩ ስራዎች ዙሪያ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር እንደዚሁም በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት እያከተከናወኑ ያሉ ተግባራት ዙሪያ ገለጻ ያደረጉላቸው ሲሆን፤ በቀጣይም ሰላምን በሚያጠናክሩ ተግባራት በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መሰል ተቋማት ጋር በትብብር  ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል። 

ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) አክለውም ኢምባሲው ወደ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በመምጣት በመጎብኘታቸው አብሮነታቸውን እና ለጋራ ግንኙነቱ የሰጡትን ትኩረት አመስግነዋል።

ክቡር ሞሐመድ ሳሌም አል-ራሽዲን የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር በበኩላቸው ስለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የልማት ስራ በማድነቅ ሰላምን የማጽናት ስራው አካል በመሆን በወንድማማችነት እና በአብሮነት በመረዳዳት አብረው መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

Tartalom megjelenítő

ቪዲዮ ዜና

ኢትዮጵያዊ ማነው? ኢትዮጵያዊነትስ ምንድነው? | የታሪክ ወግ ከኸይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) | የወል እውነት | ጋር
የጎንደር ቃልኪዳን ቤተሰብ ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ያስተላለፉት መልዕክት
አንጻራዊ ሰላምን ማፅናት
ባህላዊ የግጭት አፈታት እሴቶችን በመጠቀም የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች ሰላምን ለማስፈን የሚያበረክቱትን አስተዋፆ |selam |peace