ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ኮንፈረንስ የፎቶ ኤግዚቪሽን
Beágyazott alkalmazások
Tartalom megjelenítő
የሰላም ሚኒስቴር ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ከሚገኘው ከመሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሁማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ኮንፈረንስ ላይ ሀገራችን ያላትን የረጅም ዘመናት የሃይማኖት መከባበርና አብሮነት ለዓለም ለማሣየትና ለማስገንዘብ ያለመ የፎቶ ኢግዚቢሽን ተዘጋጅቷል ።
የፎቶው ኢግዚቢሽኑ በኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ፣ በሰላም ሚኒስቴር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም እና በሐይማኖት አባቶች ተመርቆ ተከፍቷል።
የሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ የኢትዮጵያ የሃይማኖቶች አባቶች ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ፣የክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች፣በሐይማኖት እና ሰላም ላይ ትኩረት አድርገው ጥናትና ምርምር ያካሄዱ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምስራቅ አፍሪካ፣ የሩሲያ፣ የሞሮኮ እና የደቡብ አፍሪካ የሃይማኖት ተቋማት እና አለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በኮንፈረንሱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
Tartalom megjelenítő
የክቡር የሚኒስትሩ መልዕክት
አቶ መሐመድ እድሪስ መሐመድ የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስትር
የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባራት መካከል ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ የፌዴራል ሥርዓቱ የግንኙነት ማዕከል ሆኖ ማገልገል፣ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከልና ማስተዳደር ሲሆን እነዚህን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያከናውናል።
ተጨማሪ