የሰላም ሚኒስቴር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል!
የሰላም ሚኒስቴር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል!
የሰላም ሚኒስቴር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆን ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል፡፡
በዓሉ ከሀይማኖታዊ ትውፊትነቱ በተጨማሪ ሰላምን ለመገንባት መሠረት የሆኑ ማኅበረሰባዊ እሴቶችን የሚያጎለብትና የሚያጸና፣ የሰላም አበርክቶዎችን የሚያጎላና የሚያስተሳስር፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን የሚያመጣ፤ አብሮነትን የሚያጠናክር ነው።
ስለሆነም በዓሉ በመላ ሀገራችን በሰላም እንዲከበር ከቀደምት ኢትዮጵያዊያን አባቶቻችን እና እናቶቻችን የአብሮነት ታሪክ በመማርና ለሰላም ያለንን ቁርጠኝነት ለዓለም በማሳየት በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ የጋራ ሰላማችንን እንድንጠብቅ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ ይላል። መልካም በዓል!
ሰላም ለኢትዮጵያ !