“ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!”
“ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!”
የዓድዋ ድል በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁር ህዝቦች ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ተስፋን የሰነቁበትና መነቃቃትን የፈጠሩበት ታሪካዊ ድል ነው፡፡ ይህን ድል ተከትሎ በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩ በርካታ የዓለማችን ሀገራት ከገዥዎቻቸው ነፃ የወጡበትን ቀን የነፃነት ቀን ብለው ሲያከብሩ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን የዓድዋ ጀግኖች በከፈሉልን ክቡር መስዋዕትነት ከአፍሪካ በብቸኝነት የድል በዓል የምናከብር ሀገር እንድንሆን አድርገውናል፡፡
እኛም ከአባቶቻችን የአብሮነት ታሪካችን በመማር በሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጠንክረን መስራት ይኖርብናል። የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥም ችግሮቻችንን በመደማመጥና ስልጡን በሆነ መንገድ በመነጋገርና በመፍታት አንድነታችንን ማረጋገጥ ከቻልን ዳግም ድልን በአደባባይ ማስመስከር እንችላለን፡፡
እንዲሁም የአሁኑ ትውልድ በጀግኖች ደም እረስርሳ እኛን እንዳበቀለች ተረድተን አባቶቻችን የከፈሉልንን መስዋዕትነት በማሰብ ሀገራችንን በማልማት በእድገት ጎዳና የበለጸገች ሀገር በማድረግ ማንም የማይራብባት ሀገር በማድረግ ህዝቦቿ የአፍሪካ ኩራት የሚሆኑባት ሀገር መፍጠር ይኖርብናል፡፡
ይህ ዘመን ተሻጋሪ የዓድዋ ድል በዓል ዘንድሮ 129ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ይከበራል፡፡
ክብር ኢትዮጵያን ቀና ላደረጉን ጀግኖች አርበኞች!
ሰላም ለኢትዮጵያ!