ማህበራዊ ሀብቶቻችን ለሀገራዊ ሰላም

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሀገራችን በረጅም ዘመን ታሪኳ በሕዝቦች ትስስርና ውህደት የዳበረ ማህበራዊ ሀብቶችና እሴቶች ባለቤት ናት፡፡ እነዚህ ማኅበራዊ ሀብቶች ለሰላም፤ለአንድነትና ለወንድማማችነት መጎልበት ጉልህ ሚና እንዳላቸው እሙን ነው፡፡

ማህበራዊ ሀብቶቻችን የአብሮነት፣ የሰላምና መቻቻል የትስስር ሰንሰለት ተምሳሌት ከመሆናቸው ባለፈ ለህዝቦች አብሮ መኖርና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህን ማህበራዊ ሀብቶች ለዘመናዊ ተቋማት ግንባታ መጠቀም እንድንችል እሴቶችን ከፍ ማድረግ አልቻልንም። ለዚህም በምክንያት ማስቀመጥ የሚቻለው፣ የግለኝነት አስተሳሰባችን፣ የወንዜነት አስተሳሰብ በባህላችን ውስጥ መሥረጹ የመተማመን ሰንሰለታችንን ደካማ አድርጎታል።

ስለሆነም ማህበራዊ ሀብቶቻችን ለሀገራዊ ሰላም እና ሁለንተናዊ እድገት ያላቸውን አበርክቶ ለማሳደግና ባህላዊ እሴቶቻችን ለሰላም፣ ለልማትና ዕድገት ፖሊሲዎቻችን መሰረት እንዲሆኑ ለማስቻል የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል የማኅበረሰቡን ነባር ማኅበረ-ባህላዊ ሀብቶች በመጠቀም ዘላቂ ሰላም መገንባትና ብሔራዊ መግባባትን ማስፈን አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም ለብሄራዊ መግባባት፣ ለብሔራዊ እርቅና ለሀገር ሰላም መሰረት የሆኑ ሀገር በቀል ማህበረ-ባህላዊ እሴቶችና ልማዶችን በሳይንሳዊ ጥናት በመለየት፣ በመሰነድ እና ከዘመናዊ አሰራር ጋር በማቀናጀት ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም የማህበራዊ ሀብቶቻችን መገለጫ የሆነዉን የሀገር በቀል የሽምግልና እና ፍትህ ስርዓትን የሚያሳድግና የሚያጠናክር የምክክር እና ስልጠና ስራዎችን በመስራትና የዕሴቶቻችንን ተቀባይነት በማሳደግ ማህበራዊ ሀብቶቻችንን መልሶ አቅም እንዲያገኙ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየሰራ ነው፡፡