''ሰላም  ለሁሉም ሁሉም ለሰላም'' በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የሰላም ሩጫ በሰላም ተጠናቋል

Ethiopian Date

 

Publicador de contenidos

Aplicaciones anidadas

Publicador de contenidos

ትንታኔ

አንድነትና አብሮነት ለብሔራዊ ክብር!

ቀደምት ጀግኖቻችን ችግሮችን ተፋልመው በድል ሲሻገሩ የነበሩት በመለያየት ሳይሆን በጋራ ቆመው ፈተናዎችን መመከት ስለቻሉ ነው፡፡ ችግሮችን ሲሻገሩ የነበሩት ጥብቅ የሆነ አንድነትና አብሮነት፤ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስለነበራቸው ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ፈተና ጥሏት አያውቅም!

ረጅም እና አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ፈተናዎች እየነጠረች በመዝለቋ የወዳጅም የጠላትም ትኩረት ይበልጥ እየሳበች የመጣች ሀገር እንጂ በዘመናት ውስጥ በገጠሙ ፈተናዎች ጉዞዋ ተደናቅፎ እና ወድቃ አታውቅም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

Publicador de contenidos

null ''ሰላም  ለሁሉም ሁሉም ለሰላም'' በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የሰላም ሩጫ በሰላም ተጠናቋል

ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም. መነሻውን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በማድረግ በባምቢስ ፣ በዑራኤል አደባባይ ፣ ፒኮክ መናፈሻ ፣ ሰላም መንገድ ፣ በወሎ ሰፈር ፣ ደንበል ፣ ፍላሚንጎ በማድረግ  መጨረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው የሰላም ሩጫ ተጠናቋል።

በሰላም ሩጫው ላይ ክቡራን ሚኒስትሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የውጭ ሁገር ዲፕሎማቶችና አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ እና የኃይማኖት አባቶች በሰላም ሩጫው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የሰላም ሩጫው ዓላማ በሀገራችን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም የበለጠ እንዲያጠናክር  ለማድረግ እና መላው ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ሰላም በጋራ እንዲሰሩ መነሳሳትን ለመፍጠር  ያለመ  ከመሆኑም ባሻገር እኛ ኢትዮጵያውያን ለሰላም  የምንሰጠውን ዋጋና ለሰላም ያለንን ፍላጎት  ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ መሆኑን ተገልጿል። በሩጫው በሴቶች እና በወንዶች ተወዳድረው 1-3 ላሸነፉ አትሌቶች ሽልማት ተበርክቶላቸል።

በመጨረሻ ለፕሮግራሙ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም እና በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በኩል ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የሰላም ሩጫው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በተመረጡ ከተሞች ተካሂዷል።

Publicador de contenidos

ቪዲዮ ዜና

ሰላም ለኢትዮጵያ!
ሰላም ለኢትዮጵያ!
የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም
ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም!!!