ፈተና ጥሏት አያውቅም!

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ረጅም እና አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ፈተናዎች እየነጠረች በመዝለቋ የወዳጅም የጠላትም ትኩረት ይበልጥ እየሳበች የመጣች ሀገር እንጂ በዘመናት ውስጥ በገጠሙ ፈተናዎች ጉዞዋ ተደናቅፎ እና ወድቃ አታውቅም፡፡

የገጠሟት ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች ቀደምቶቹ ኢትዮጵያዊያን የማያቋርጥ ድልና ጀብዱ በመፈጸም ገናና የሆኑ አዳዲስ ታሪኮችን እንዲያስመዘግቡ ያስቻለ እንደመሆኑ ፤ አሁንም እየገጠማት ያለው ፈተና ለአሁኑ ትውልድም የራሱን ታሪክ ሠርቶ የጽናት ተምሳሌት እንዲሆን ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡

ቀደምት ኢትዮጵያዊያን ሀገር ፈተና በገጠማት ጊዜ ያሳዩት ጽናት፣ አንድነት፣ አብሮነት እና ለሀገር የከፈሉት መስዋዕትነት ኢትዮጵያን በዓለም ላይ ልዩ ተጠቃሽ እንድትሆን ካደረጓት ልዩ ታሪኮቿ ውስጥ እንደ አንዱ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡

በየዘመኑ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በድል ለመሻገር ብሎም ሀገር በጠንካራ መሠረት ላይ እንድትገነባ በተለይም ደግሞ ሀገር ከውስጥና ከውጭ፤ ከጎረቤቶቿም ጭምር የሚመጡትን ችግሮች በመመከት ሉዓላዊነቷን ማስጠበቅ የምትችለው የዜጎች አንድነት፣ ኅብረት፣ አብሮነትና ትብብር ተጠናክሮ ለጋራ ቤታችን ለሆነችው ኢትዮጵያ ለሰላሟ እና ለሉዓላዊነቷ በጋራ ስንቆም ነው፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !