የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሀገራዊ የምክክር መድረክ አካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ግንቦት 22 ቀን 2016 . የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት " በሚል መሪ ቃል ዘላቂ የሠላም አንድነትን በሚገነባ እና ጠንካራ የውይይት ባህልን በሚያዳብር መልኩ ስኬታማ ሀገራዊ የምክክር መድረክ አካሄዷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲዉ ኮማንዳንት ብርጋዲየር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ ቀለመ ብዙ ሃምራዊ የሆነች ታሪካዊ ሀገራችን በትብብርና በጋራ ሰላሟንና ህብረ ብሔራዊ አንድነቷን በመገንባት በሉዓላዊ ነፃነቷ ላይ ተመራጭና ተፈላጊ ሆና እንድትቀጥል ለማድረግ የሁላችንም የነቃ ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሠራዊታችን ሀገሩን ከማፍቀር በላይ ለወገኑ ነፃነትና ክብር ሲል የህይወትና የአካል መስዋትነት ጭምር በተግባር እየከፈለ ሀገር እያዳነ ነው ያሉት ጄኔራል መኮንኑ ዜጎች ህብረ ብሔራዊ አንድነታቸውን አጠናክረው በሃገራቸው ማንነት ላይ ያላቸውን ግንዘቤ የበለጠ ማጎልበት የሚያስችል የውይይት ባህልን ማዳበርና መለማመድ አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የምክክር መድረኩን የመሩት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ሮባ ጴጥሮስ የብሔር እሳቤ ብሄራዊ ጥቅምን ማረጋገጥ እንደማይችል በሃሳባቸው አጠናክረው ሁላችንም እንደ ዜጋ ከእኔነት የአስተሳሰብ ትርክት በመውጣት ለህብረ ብሄራዊ አስተሳሰባችን መድህን በመሆን ታላቋ ሀገራችን በአንድነት የተገመደች በህብር የተፈተለች መሆኗን ደግመን ደጋግመን በእውነተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት እያረጋገጥን መቀጠል አለብን ብለዋል፡፡ 

እንደ ሃገር የተሻለ ሰላምና ጠንካራ ህብረ ብሄራዊ አንድነት እንዲረጋገጥ የሁላችንም ሃላፊነት ወሳኝ ነው ያሉት የህግ አስተማሪው ለሃገራችን የእድገት ጉዞ እና የጋራ ማንነት ላይ ጊዜውን የሚመጥን ዘላቂ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ በሃገር ፍቅር የደመቀ ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት ነው በማለት አስምረውበታል፡፡ 

ጊዜው አገራችን ስለ ሰላምና አንድነት አብክራ እየመከረችበት ያለ ወቅት ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች እኛም በበኩላችን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለሃገር ሰላምና አንድነት ስንል በንፁህ አዕምሮና በቅን ልቦና ሆነን ጊዜና ሁኔታ ሳይገድበን የድርሻችንን በትጋት መስራት እንዳለብን በምክክር መድረኩ ላይ ተገንዝበናል ብለዋል፡፡