''መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ሥራዎች መካከል የብሔረ መንግስት ግንባታ አንዱ ነው'' - ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መስከረም 10/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር “ማህበራዊ ትስስራችን ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን'' በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ማብሰሪያ የውይይት መድረክ ተጠናቋል።

ውይይቱን በንግግር ያጠቃለሉት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ሥራዎች መካከል የብሔረ መንግስት ግንባታ አንዱ መሆኑን አንስተዋል።

የጋራ ማንነትን ለማጎልበት እና የብሔረ መንግስት አስተሳሰብን ለማጠናከር ትምህርት ቤት ቁልፍ ሚና ይጫወታል ያሉት ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በዩኒቨርስቲዎች የተጀመረው የቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት ይህን ለማሳከት ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና በማህበረሰቡ መካከል የተጀመረው የቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት እየተሸረሸረ የመጣውን ማህበራዊ እሴት መልሶ ለመገንባት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) አክለውም የሰላም ሚኒስቴር ማህበረ-ባህላዊ ሀብቶችን እንደ አንድ የዘላቂ ሰላም ዕሴት ግንባታ በመጠቀም የተሸረሸሩ ማህበረ-ባህላዊ ሀብቶቻችን ተመልሰው እንዲያንሰራሩ በማድረግ ለሰላም እና ለሀገር ግንባታ እንዲውሉ ስልቶችን በመቀየሰ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክትን ለጀመሩ ዩኒቨርስቲዎችና ከተማ አስተዳደሮች የማበረታች የዕዉቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል።