በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ ማህበራዊ ትስስራችን ትልቅ ቦታ አላቸው - ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መስከረም 10/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር “ማህበራዊ ትስስራችን ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን'' በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ማብሰሪያ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የዛሬው የውይይት መድረክ ዓለማ ጎንደር ዩኒቨርስቲ የጀመረውን የቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት በሌሎች መንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙባቸው ከተማ አስተዳዳሪዎች በመውሰድና ዕቅድ በማውጣት ወደ ሥራ የገቡትን ለማበረታታት እና በይፋ ሥራው መጀመሩን ለማብሰር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ከማህበረሰቡ ጋር በማገናኘት ተማሪዎች የሌላውን ባህል፣ ቋንቋ፣ እምነት እና እሴቶች ከቃል ኪዳን ቤተሰቦች እንዲማሩ በማድረግ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጎልበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ይህንን ፕሮጀክት ወደ ሌሎች የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በማስፋት በተመረጡ በጎ ፈቃደኟ አዲስ ገቢ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና በከተማ ነዋሪዎች መካከል እውነተኛ የሆነ ቃል ኪዳን ቤተሰብነት ትውውቅ እና ትስስር እንዲፈጠር እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ ማህበራዊ ትስስራችን ትልቅ ቦታ አላቸው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴዔታው ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ማህበረ-ባህላዊ ሀብቶችን እንደ አንድ የዘላቂ ሰላም ዕሴት ግንባታ በመጠቀም የተሸረሸሩ ማህበረ-ባህላዊ ሀብቶቻችን ተመልሰው እንዲያንሰራሩ በማድረግ ለሰላም እና ለሀገር ግንባታ እንዲውሉ ስልቶችን በመቀየሰ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ ላይ «ማኀበራዊ ትስስር ለህብረ ብሔራዊ አንድነታችን» የሚል ሰነድ በዶ/ር ሮባ ጴጥሮስ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ፣ የክልሎች ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊዎች፤ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙባቸው የከተማ አስተዳዳሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት መድረኩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።