የ14ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ተጀመረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ በ14 ኛው ዙር መርሃ ግብር ስልጠናቸውን ለመከታተል በጅማ፣ በሐዋሳ፣ በወሎ፣ በወልቂጤ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች የገቡ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኝ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው።

የሰላም ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሳተፍ በሥነ ምግባር፣ በክሕሎት እና በሥራ ፈጠራ ግንዛቤ የሚያዳብር ስልጠና በመስጠት እና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በማሰማራት የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ፕሮግራሙ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቀሰሙትን ዕውቀት እና የተለያዩ ሙያ ከተሰጣቸው ስልጠና ጋር በማስተሳሰር በበጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት በዜጎች መካከል ማኅበራዊ ትስስር እንዲጎልብት፣ሀገራዊ አንድነትና አብሮነት እንዲጠናከር በማድረግ አዎንታዊ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱበት ነው፡፡

"በጎነት ለአብሮነት በሚል መሪ ሐሳብ በሰላም ሚኒስቴር የተጀመረው የወጣቶች በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ዓላማ የወጣቱን አመለካከት፣ ክህሎትና ሞራል በመገንባት እንዲሁም አንዱ የሌላውን ባህልና እሴት እንዲያውቅ በማድረግ ፤ በማንነቶች ላይ መሠረት አድርጎ ያለውን መጠነኛ መከፋፈልና ጥርጣሬ በማስወገድ የሀገራችንን ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት ማረጋገጥ ነው።