የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በህዝበ ሙስሊሙ የነቃ ተሳትፎ በመጠናቀቁ ለዕምነቱ ተከታዮች እንኳን ደስ አላችሁ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ እሰልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጠቅላላ ምርጫውን አጠናቋል።

ህዝበ ሙስሊሙ መሪውን በድምፁ በመምረጥ ተቋሙን በነፃነት ለመምራት ለዘመናት ሲታገል የቆየ ሲሆን ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው መልካም ዕድል ጠቅላይ ም/ቤቱ በአዋጅ ሊቋቋም ችሏል። በዚህ መነሻ ህዝበ ሙስሊሙ በነፃነት ለቀጣይ አምስት ዓመታት ተቋሙን የሚመሩ መሪዎችን በነቃ ተሳትፎ፣በብልህነት፣በከፍተኛ ሀገራዊ ስሜትና ሀላፊነት፣ አካታችና የመላው ህዝባችንን ሰላምና ሀገራዊ የአብሮነት መንፈስን በሚያጠናክር መልኩ በመጠናቀቁ የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን።

በየደረጃው ተቋሙን ለመምራት ኃላፊነትን ከተረከቡት የዕምነቱ አባቶች ጋር ተቀራርበን እንደምንሠራ እየገለጽን፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሰላም፣ በማኅበራዊ ልማት እና በሀገር ግንባታ ዙሪያ የጀመረውን በጎ ተግባርን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን።

የሰላም ሚኒስቴር

ጳጉሜ 2/2017

አዲስ አበባ